- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ተኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት
Bid Opening Date: ጨረታው በ16ተኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡45
Published On: አዲስ ዘመን (Sep 22, 2023)
Bid document price: 100.00 ብር
Bid bond: Null
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ለፖሊስ መምሪያ እና ለኢንተርፕራዞች ኢን/ልማት መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ባቀዱት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ ውስጥ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት: -
1. የሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ፣ ሎት/ምድብ 01/2016
2. የሀዋሳ ከተማ አስ/ፖሊስ መምሪያ ፣ ሎት/ምድብ 02/2016
3. የሀዋሳ ከተማ አስ/ኢንተርፕራዞች ኢን/ልማት መምሪያ ፣ ሎት/ምድብ 03/2016 ለቢሮ አገልግሎት እንድንከራይላቸው የጠየቁን ጽ/ቤትና መምሪያዎች ባቀረቡት መመዘኛ በሰነድ በተቀመጠው መሠረት የሚያሟሉትን ሕንፃዎችን የሚያቀርብ አቅራቢ መወዳደር ይችላል።
01. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
02. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ሲሆን፤
03. ተጫራቾች የ2015 ዓ.ም ድረስ የጣራ ግርግዳና የዓመቱ የቦታ ግብር የገበረበት ማስረጃ ማያያዝ አለበት።
04. የአከራይ ተከራይ ግብር መከፈሉን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማያያዝ አለበት።
05. የጨረታ ሰነዱ ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሂደት) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
06. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሽገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጂናልና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ጨረታውን በግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
07. ጨረታው በ16ተኛው አሥራ ስድስተኛው/ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ በ3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
08. በተሸጠው ሰነድ ዋጋውን ሞልቶ ያስገቡ ፤ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
09. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ
ሀዋሳ
Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መም
Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
| |||||||
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets