- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት
Bid Opening Date: በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:30
Published On: አዲስ ዘመን (Sep 28, 2023)
Bid document price: 200.00 ብር
Bid bond: 10,000.00 ብር
Region: Sidama
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በ2016 በጀት ዓመት ለሀገረ-ሰላም አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ40 ሰልጣኞች የምግብ አቅርቦት ግዥ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሆኖ በየሶስት ወር አፈጻጸም እየታየ የሚታደስ ውል በመግባት የአገልግሎት ግዥውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች፣
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) በላይ ሲሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) እየከፈሉ ከመ/ቤቱ ግዢ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፣
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን 10,000.00 (አስር ሺህ) በጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ጨረታው በሁለት ፖስታ የሚቀርብ ሲሆን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ መቅረብ አለበት ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 15ተኛው ቀን 8:00 ሰዓት ድረስ በመ/ቤቱ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8:30 የሚከፈት ይሆናል፣
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ስማቸውንና ፣ ፊርማቸውን ፣ አድራሻቸውንና ስልክ ቁጥር ማስፈር አለባቸው።
7. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ግዜ የግዥውን ብዛት (መጠን/ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ / ለመጨመር) መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የምግብ አይነት መ/ቤቱ ባቀረበው የምግብ ሜኑ ዝርዝር መሰረት ብቻ ነው መወዳደር የሚችሉት።
9. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 221 6730 /046 220 1267 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የመ/ቤቱ
አድራሻ፡ ከኢሚግሬሽን ፊት ለፊት/ ከሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ግቢ ውስጥ ነው።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን
National Regional Government Sports Commission የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ስፖርት ኮሚሽን
|
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets