- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: Oct 25, 2023 12:00 PM
Bid Opening Date: Oct 25, 2023 2:00 PM
Published On: አዲስ ዘመን (Oct 04, 2023)
Bid document price: 100.00 ብር
Bid bond: 2%
Region: Oromia
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለአዳማ ወረዳ አስተደደር ጽ/ቤት ሥራ ያቆመው የሁዋይ ሲሚንቶ ፋብሪካን ከተተከለበት ቦታ በባለሙያ አወዳድሮ ማስነሳትና ወደሚያስቀምጥበት ቦታ ማጓጓዝ ስለሚፈልግ በዚህ ሙያ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማስነሳት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ሥራ የተሰማራችሁና ሙያ ያላችሁ ከዚህ በታች ያለውን መስፈርት የምታሟሉ ሙያተኞች ሁሉ ግልጽ በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ ትችላላችሁ።
1. በዚህ ሥራ ላይ የተሰማራና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የ2015/6 ያለው፣
2. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችል፣
3. የዘመኑን የመንግሥት ግብር የከፈለ፣
4.ማሽን በመትከልና በማደስ የሙያ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታው ፖስታ ላይ የተጫራች ሙሉ አድራሻ ፣ የድርጅቱ ማሕተም እንዲሁም ጨረታውን ያወጣው መሥሪያ ቤት አድራሻ እና የፕሮጀክቱን ስም መጥቀስ አለበት።
7. አሸናፊው ድርጅት እቃውን ከቦታው ካነሳ በኋላ በራሱ ወጪ የሚቀመጥበት ቦታ ማድረስ አለበት።
8. አሸናፊው ድርጅት የተፈታው እቃ ቢበላሽ ወይም ቢጐድል በራሱ ወጪ የመተካት ግዴታ አለበት።
9. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፕኦ ማስያዝ አለበት።
10. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 በመክፈል ከአዳማ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ) የተዘጋጀው ሰነድ ገዝተው መወዳደር ይችላሉ።
11. የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
12. ፋብሪካው የሚገኝበት አዱላላ አጤ አሮሬቲ ቀ/ገ/ማህበር ከአዳማ ከተማ በግምት 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይሆናል።
13. የተነሳው የፋብሪካ ዕቃ የሚጓጓዝበት ዕቃው ከሚገኝበት ከአዱላለ አጤ አሮሬቲ ቀ/ገ/ማህበር እስከ ቀጨማ ቀ/ገ/ማህበር በግምት 15 ኪሎ ሜትር ይሆናል።
14. ጨረታው የሚዘጋው በ14/2/2016 ዓ.ም በ6:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8:00 ሰዓት ተጫራቾች በሚገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-ተወዳዳሪው ባለሙያው የሚያሰራበትን ዋጋ ታሳቢ አድርጐ ዋጋውን መሙላት አለበት።
ለበለጠ መረጃ፡- አዳማ ወረዳ ገ/ጽ ቤት
ስልክ ቁጥር 022 112 7908/0913 23 02 09/0913 24 14 11
አድራሻ- አዳማ መብራት ኃይል ንግድ ም/ቤት አዳራሽ ፊት ለፊት
የአዳማ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets