- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: በ6ኛው ቀን በግልፅ ጨረታ ጠዋት 4፡00 ሰዓት
Bid Opening Date: በ6ኛው ቀን በግልፅ ጨረታ ጠዋት 4፡05
Published On: አዲስ ዘመን (oct6, 2023)
Bid document price: 100
Bid bond: 5%
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታቂያ ቁጥር 12/2016
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የተተውና ተወርሰው የሚገኙ
1.መገናኛ መሣሪያ ፣
2.የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
3.የመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ ፣
4.የሞተር ሣይክል መለዋወጫ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
1.የጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ግምታዊ ዋጋው ከብር 500ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም
ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ኢያስፈልግም።
2.ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት
ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት
ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ፣ ቅዳሜ ከ2:00 እስከ-6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ
የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል በቅ/ጽ/ ቤቱ ከገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
3.ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን
ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO፣ የጨረታ ሰነድ እና
አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
4.ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ
5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የንብረቶቹን ናሙና በመደበኛ የሥራ ሰዓት በሀዋላ ማዕከላዊ
መጋዘን ማየት የሚችሉ ሲሆን፤ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው
(ስድስተኛው) ቀን በግልፅ ጨረታ ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡05 ሰዓት በአዲሱ መጋዘን ይካሄዳል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይሆናል።
5.ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ
በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫት በሚለው
መስመር በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
1.ማንኛውም የግልፅ ጨረታ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን
ዋጋና መግለጫ መለወጥ እና ማሻሻል አይችልም፡፡
2.ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
3.ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
4.በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው
ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
5.ተጫራቾች ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ቢሰጡና ችግር ቢፈጠር ቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
6.ለጨረታው የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ ነው፡፡
7.አሸናፊዎቹ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሰርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ላይ ይወጣል፡፡
ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046 212 5396
የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
የሀዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets