- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: በ15ኛው ቀን /ተከታታይ ቀናት/ 6፡00 ሰዓት
Bid Opening Date: በ15ኛው ቀን /ተከታታይ ቀናት/ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
Published On: አዲስ ዘመን (Oct 08, 2023)
Bid document price: 200.00 ብር
Bid bond: 30,000.00 ብር
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2016
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2016 በጀት ዓመት የፈሳሽ ናይትሮጂን ማሽን መለወወጫ ዕቃ እና ዘንደር /ዘመናዊ/ የንብ ቀፎና የሽግግር ቀፎ ሕጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች -
1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ መሣተፍ የሚችሉና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 /አስራ አራት/ ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከሳውዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፍ ብሎ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 በአካልም ሆነ በተወካዮቻቸው አማካኝነት መግዛት ይችላሉ።
3. በየዘርፉ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (Bank Guarantee) ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPD) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
5. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የቴክኒካልና የፋይናንሻል ኮፒና ኦሪጅናል ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን /ተከታታይ ቀናት/ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት ያግደውም።
6. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም ሳያደርግ ያቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
8. የጨረታው መዝጊያና መከፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
9. ከሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916 10 83 60/ 0916 07 00 57 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- ከሳውዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፍ ብሎ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 እንገኛለን፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት እንስሳት
ሀብት ልማት ቢሮ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ
Address | ከሳውዝ ኢንተርናሽናል ሆቴል ከፍ ብሎ ደቡብ ግሎባል ባንክ ባለው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 08 |
---|---|
Mobile |
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets