- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡15
Bid Opening Date: በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡45
Published On: አዲስ ዘመን (Oct 09, 2023)
Bid document price: 200.00 ብር
Bid bond: 50,000.00 ብር
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራከሽን መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት ግዥ ባቀዱት መሠረት የቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚሰጥ ዘይትና ማለስለሻ ቅባት እና ባትሪዎች ግዥን ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ለተሽከርካሪዎች የተለያዩ ዓይነት ዘይትና ማለስለሻ ቅባት፣ ሎት 01/2016
2. የተሽከርካሪዎች ባትሪ፡- ሎት 02/2016
በዚህ መሠረት፡-
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።
1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ /የተመሰከረ/ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
6. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው ሲታሸግ ኤንቨሎፑ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በፋይ/ኢኮ/ልማ/መምሪያ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 /ግዥ ኬዝ ቲም/ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 3፡15 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከቀኑ 3፡45 ሠዓት በቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል። ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል። የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውንሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 22 1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
ሀዋሳ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
Phone | |
---|---|
Mobile | +251 91 198 4331 |
Fax | +251 46 221 4902 |
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets