- Agriculture & Food
- Beauty & personal care
- Books
- Electronics
- Fashion
- Furniture
- Luggage and Travel Gear
- Office supplies & Services
- Sports & Tools
Help & Settings
Customer Service
Sign In
Bid Closing Date: ለ21 (ሃያ አንድ) ቀናት ክፍት ሆኖ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
Bid Opening Date: በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
Published On: Reporter
Bid document price: 200
Bid bond: 2%
Region: Sidama
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2016
ታቦር ሴራሚክ ውጤቶች አ.ማ ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የፋብሪካ ቅጥር ግቢ ይዘቱ 32064
ካሬ ሜትር ስፋት ቦታ አስገንብቶ ለሚገኘው የፖርስሊን ፋብሪካ ሼድ ከጣሪያ የሚወርድ
የዝናብ ፍሳሽ ውሃ ከሼድ ውስጥ ወደ ውጭ እና ከውጭ አስፈላጊ በሆኑ የተመረጡ ቦታዎች
በሚገነባ ማንሆል (MAN HOLE) ተሰብስቦ ከነባሩ ጋር የማገናኘት በድንጋይ እና ሺር ዎል
(Shear Wall) በአሰሪው የግንባታ ግብዓት አቅራቢነት ስራውን አስፈላጊውን በቂ የሥራ
መሳሪያና የሰው ሃይል ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል
በቁርጥ ዋጋ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታ ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት በግንባር ሀዋሳ
በፋብሪካው ግቢ ተገኝተው የግንባታ ሳይቱን ማየት የስራውን ዝርዝር መረጃ እና የቀረበው
ማቴሪያል መመልከት ይጠበቅባቸዋል።
በዚሁ መሠረት
1.በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ደረጃ GC7 እና በላይ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ::
2.በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ወረቀት እና
የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ 3.የተጨማሪ
እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
4.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የሚሆን ከሚያቀርቡት የቁርጥ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO በታቦር ሴራሚክ
ውጤቶች አ.ማ ስም ማስያዝና ከጨረታው ሰነድ ጋር ኦርጅናሉ በስም ታሽጎ በኤንቨሎፕ
ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5.ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይቱን እና ለግንባታ የቀረበውን
ማቴሪያል በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
6.የሥራ ተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፍቃዳቸውንና የተጨማሪ እሴት ታክስ (AI)
የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክሜንቱን ይህ ማስታወቂያ
ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 21 (ሃያ አንድ) የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 29 በመቅረብ የተዘጋጀውን ሠነድ በመግዛት በጨረታው
ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
7.ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 (ሃያ አንድ) ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል። ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ለዚሁ አገልግሎት
በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለትና ቀን በ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
22ኛው ቀን እሁድ ወይም በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
8.አሸናፊ ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ በተጠቀሰው ሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ
የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
9.የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ዋስትና
(CPO) ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በስም ታሽጎ በማያያዝ ፤ ፋይናንሻል (የቁርጥ ዋጋ ሰነድ)
አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና አንድ ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና አንድ ኮፒ
በተለያዩ ኢንቮሎፕ በመምራት በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማኖር ከላይ በተጠቀሰው ቀንና
ስዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10.ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 0939-47-48-47/0911-65-87-18/
0901-51-76-59 /0966- 75-93-511 / 046-220-2352/046-220-1166 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ::
የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት አድራሻ አ/አ ጉርድ ሾላ ታቦር ሴራሚክ ፒካን
ህንፃ 2ኛ ፎቅ እና በሀዋሳ ከተማ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 28 ነው::
ታቦር የሴራሚክ ውጤቶች አ.ማ
Tabor seramic
Merkatomarket is your go-to online marketplace for all your needs. We provide a wide range of products with the best deals and customer service.
© 2024 merkatomarket.com. All rights reserved.
powered by Bet softnets